ዲሞክራሲ (ነፃነት) ከኢኮኖሚ እድገት በኋላ ወይስ በፊት?
የሰው ልጅ ከሌሎች የፈጣሪ ፍጡራን በተለየ ከታደለው ፀጋ ውስጥ አንዱ ስልጣኔ ናፋቂነትን ነው፡፡ ምን አይነት ስልጣኔ የሚለውን ጥያቄ ለጊዜው እንተወውና የሰው ልጅ የዝግመተ እድገት ታሪክ የሚያሳየን አለም አሁን ለደረሰችበት የሀያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ስልጣኔ መንስኤው ስልጣኔ ናፋቂ የሆነው የሰው ልጅ በየዘመኑ ያከናወናቸው እንቅስቃሴዎች ድምር ውጤት መሆኑን ነው፡፡
የሰው ልጅ ከሌሎች የፈጣሪ ፍጡራን በተለየ ስልጣኔ ናፋቂ የሆነበት ምክንያት ደግሞ ከሌሎች ፍጡራን በተለየ ፈጣሪ የቸረው የማሰብ ፀጋው ነው፡፡ ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙላት እንዲል ቃሉ የሰው ልጅ ዘር መብዛቱን ተከትሎ እንደ ህዝብ በቡድን መኖር ከመጀመሩ ጋር በተያያዘ የጋራ የሆነን ሀብትን ለመጠቀምም ሆነ እንደ ግለሰብ ለሚያደርገው እንቅስቃሴ ፍትሀዊነት ህግ እና ደንብን ማእከል ያደረገ መንግስታዊ ስርአት ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረ ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡ ይህም ለስልጣኔ መንስኤ የሆነው ከፈጣሪ የተቸረውን የማሰብ ነፃነት በመንግስታዊ ስርአቱ ላይ የተንጠለጠለ እንዲሆን አድርጎታል፡፡
የሰው ልጅ ከሌሎች የፈጣሪ ፍጡራን በተለየ ስልጣኔ ናፋቂ የሆነበት ምክንያት ደግሞ ከሌሎች ፍጡራን በተለየ ፈጣሪ የቸረው የማሰብ ፀጋው ነው፡፡ ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙላት እንዲል ቃሉ የሰው ልጅ ዘር መብዛቱን ተከትሎ እንደ ህዝብ በቡድን መኖር ከመጀመሩ ጋር በተያያዘ የጋራ የሆነን ሀብትን ለመጠቀምም ሆነ እንደ ግለሰብ ለሚያደርገው እንቅስቃሴ ፍትሀዊነት ህግ እና ደንብን ማእከል ያደረገ መንግስታዊ ስርአት ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረ ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡ ይህም ለስልጣኔ መንስኤ የሆነው ከፈጣሪ የተቸረውን የማሰብ ነፃነት በመንግስታዊ ስርአቱ ላይ የተንጠለጠለ እንዲሆን አድርጎታል፡፡
የኢኮኖሚ እድገት ሂደት ሲሆን በዚህ ሂደት ውስጥ ከሚከወኑ ክንውኖች ውስጥ በኢኮኖሚ መሻሻል ስፋት ልክ የህብረተሰቡ ኑሮ መሻሻል ዋነኛው ነው፡፡ ከላይ በጠቀስኩት ምክንያት የማሰብ ነፃነት በመንግስታዊ ስርአቱ ላይ የተንጠለጠለ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ትልቁ ጥያቄ እና ክርክር በኢኮኖሚ እድገት ሂደት ውስጥ ነፃነት እና የኢኮኖሚ እድገቱ አብረው ነው መጓዝ ያለባቸው ወይስ አንዱ መቅደም አለበት የሚለው ሆኑአል፡፡
በዲሞክራሲያዊ ስርአት መንግስት ውስጥ ነፃነት እስኬት ይሄዳል?
የዲሞክራሲያዊ ስርአትን አይነት ወደ ጎን ትተን በሁሉም ዲሞክራሲያዊ ስርአት ውስጥ የነፃነት መገለጫን ስናይ፣ በዲሞክራሲያዊ ስርአት ዋነኛ ማእከል የብዙሀኑ ፍላጎት የሚገዛበት ሆኖ፣ በየትኛውም አይነት ዲሞክራሲያዊ ስርአት ጥበቃ የሚደረግላቸው መብቶች ውስጥ የግለሰቦች የመፃፍ፣የመናገር፤ በነጻነት የመደራጀት፤ ያለምንም ገደብ የመንቀሳቀስ፤ እንደ ግለሰብ የፈለገውን እምነት የማመን፤ በተመቸው ቋንቋ የመናገር ፣ እንደ ግለሰብ የራስን ህይወት ለማሸነፍ የሚደረግን እንቅስቃሴ አለማስተጓጓልን፣ እንደ ግለሰብ ጠሮ ያፈራውን ንብረት ያለመነጠቅ፣ ባጠቃሊይ ለዜጎች የተሰጡ መብቶችን ሳይነኩ በግለሰቡ፣ በልጁ... ወዘተ ፣ ባጠቃሊይ በቤተሰቡ ጉዲይ ላይ ውሳኔ የመስጠት መብቱን።
በአንድ ወቅት በብዙሀኑ ድምፅ ተበልጠው አናሳ አመለካከት የያዙ ሰዎች፤ እነኝህን መብቶች ተጠቅመው አመለካከታቸውን የብዙሀኑ ለማድረግ የመሞከርና በሕግ በተቀመጠው የምርጫ ስነስርዓት ተጠቅመው የቀድሞውን የብዙሀን መንግስት ቀይረው እነሱ ብዙሀን የመሆን ሙከራ የማድረግ መብቶች ናቸው፡፡
በተጨማሪም በየትኛውም አይነት ዲሞክራሲያዊ ስርአት ጥበቃ የሚደረግላቸው መብቶች ውስጥ በፈቃደኝነት የተመሰረቱ የወል ስብስቦች (የሀይማኖት፣ የብሄር፣ የባህል፣የሞያ ስብስቦች ወዘተ) ባጠቃላይ የማህበረሰቡን እና የሌሎች ዜጎችን መብቶች በማይነካ መልኩ እስከ ተደራጁ ድረስ የጋራ ጉዳያቸውን ያለማንም ጣልቃ ገብነት ያለማካሄድ.ባህላቸውንና እምነታቸውን የመከተል እና በፍቃደኝነት የሚቀበላቸው እስካገኙ ድረስ የማስፋፋት፣ የውስጥ ጉዳያቸውን የሚያካሂዱበትን የራሳቸውን ህግ እና መዋቅር የመዘርጋት፣በሚመቻቸው መንገድ ተደራጅተው በጋራ በተቀመጠው ህግ መሰረት የጋራ ጥቅሞቻቸውን ለማስጠበቅ የመንግስትን የጋራ ውሳኔ ለማግባባት መሞከርን፣ በተቀመጠው ህግ መሰረት አቤቱታ የማቅረብ፣ ባደባባይም ተቋውሞ የመግለፅ መብቶችን ያካትታል፡፡
ይህም በእኔ እምነት ነፃነት ለኢኮኖሚ እድገት መንስኤ ነው ወይስ ነፃነት ከኢኮኖሚ እድገት በሁአላ ነው መምጣት ያለበት የሚለውን ለመፈተሸ የዲሞክራሲ ስርአትን ማእከል በማድረግ የማየትን አስፈላጊነት አሳይ ይመስለኛል፡፡
ዲሞክራሲ እና የኢኮኖሚ እድገት የአንድ ሳንቲም ግልባጭ ወይስ የተነጣጠሉ ?
ዲሞክራሲ እና የኢኮኖሚ እድገት የአንድ ሳንቲም ግልባጭ ወይስ የተነጣጠሉ ?
በድህነት የሚኖሩ ህዝቦች ቢያንስ መሰረታዊ ፍላጎታቸውን እስኪያሟሉ ድረስ የነፃነት እና የዲሞክራሲ ጥያቄ ሁለተኛ ነው ብለው የሚሞግቱ ሰዎች ረሀብ፣በሽታ ድንቁርና መገለጫቸው የሆኑ ደሀ ሀገራት ከምንም በፊት ትኩረት ሊሰጡ የሚገባው የኢኮኖሚ እድገትን ማፋጠን ላይ መሆኑን በመግለፅ ነፃነት እና የዲሞክራሲ የሚያስፈልገው የኢኮኖሚ እድገቱ የሆነ ደረጃ ላይ በመድረስ ነፃነትን ለማጣጣም የሚችል እና ነፃነትን ማእከል ያደረገ ማህበረሰብ ሲፈጥር ብቻ ስለ መሆኑ ይሞግታሉ፡፡
እንደዚህ ፅሁፍ አቅራቢ ሁሉ ያለ ነፃነት ኢኮኖሚ እድገት የማይታሰብ ነው ብለው የሚሞግቱ ሰዎች የሚያቀርቡት ምክንያት የኢኮኖሚ እድገት ሊኖር የሚችለው ነፃ በሆኑ ግለሰቦች እንቅስቃሴ መንስኤነት መሆኑን ነው፡፡
አለም አቀፍ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት እርዳታን እና ብድርን ተቀብለው የህዝባቸውን ኑሮ ባሻሻሉ እና ባላሻሻሉ የአፍሪካ ሀገራት መሀል ያለው ልዩነት መንስኤው በሀገራቱ መንግስታዊው ስርአት ውስጥ ያለው የተጠያቂነት እና የመልካም አስተዳደር ልዩነት መሆኑን ሲሆን፣ ይህም በእኔ እምነት የሚያመላክተው ነፃነትን በማረጋገጥ ተጠያቂነት ያለው መልካም አስተዳደር ለሰፈነበት መንግስታዊ ስርአት መንስኤ የሚሆነው ዲሞክራሲ ለኢኮኖሚ እድገት ምክንያት ስለመሆኑ ሲሆን፣ በተጨማሪም ዲሞክራሲ ከኢኮኖሚ እድገት በሁአላ ነው ለሚለውን መከራከሪያ ዋጋ ቢስ ስለመሆኑ ያመላክታል፡፡
በዲሞክራሲያዊ ስርአት ውስጥ የሚገነባው ጠንካራ እና ነፃ ፕሬስ ውስን የሆነውን ሀገራዊ ሀብት ለኢኮኖሚ እድገት በሚል የዳቦ ስም የግላቸው ጥቅም የሚያውሉ ባለስልጣናትን በማጋለጥ መንግስታዊ ሌብነትን በመከላከል ረገድ ያለው ድርሻ ሌላኛው የዲሞክራሲ እና የኢኮኖሚ እድገትን አይነጣጠሌነት አመላካች ነው፡፡
ለኢኮኖሚ እድገት ዋናው መንስኤ ምርታማነት ሲሆን ለምርታማነት ምክንያት ከሆኑት ውስጥ አንዱ የሰው ሀይል ነው፡፡ የሰው ሀይልን ለምርታማነት መንስኤ እንዲሆን ያደረገው ጉልበቱ ብቻ ሳይሆን ከጉልበቱም በላይ የማሰብ ተሰጥኦው ነው፡፡ ለምርታማነት መንስኤ የሆነው የሰው ሀይል የማሰብ ሀይሉን አበልፅጎ ለምርታማነት ምክንያት እንዲሆን ዋነኛው ግብአት ደግሞ ነፃነት ነው፡፡
የሰው ልጅ ያለማንም ተፅእኖ የማሰብ ነፃነቱ ሲዳብር አዳዲስ ሀሳቦችን የማፍለቅ ችሎታው፣አዳዲስ አሰራር የመጠቀም ድፍረቱ ባጠቃላይ ለሰምርታማነት ያለው ተነሳሽነቱ ይዳብራል በሌላ አነጋገር ለኢኮኖሚ እድገት መንስኤ ይሆናል እንደማለት ሲሆን፣ ይህም ከምንም በላይ የሰው ልጅ ተፈጥሮ በራሱ ዲሞክራሲን እና የኢኮኖሚ እድገትን አንድ ላይ ለማስኬድ እንጂ ኢኮኖሚ እድገትን በማስቀደም ዲሞክራሲን በኋላ ለሚል ንድፈ ሀሳብ ምቹ ስለ አለመሆኑ አሳይ ከመሆኑም በላይ መጀመሪያ ድህነትን እንቅረፍ ዲሞክራሲ በሂደት ነው የሚለው ብሂል የአንባገነኖች መቆመሪያ ስለመሆኑ አሳይ ነው፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ በእኔ እምነት የኢኮኖሚ እድገት ሊኖር የሚችለው ነፃ በሆኑ ግለሰቦች እንቅስቃሴ መንስኤነት የመሆኑን እውነትነት ማረጋገጫ ነው ፡፡
የኢኮኖሚ እድገት ሊኖር የሚችለው ነፃ በሆኑ ግለሰቦች እንቅስቃሴ ብቻ ነው!
Comments
Post a Comment
Thank You!!