በአንድ ወቅት የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጠኛ ንጉሳችንን ቀ. ኃይለሥላሴን እንዲህ ሲል ይጠይቃቸዋል...
 “ለመሆኑ ኢትዮጵያዊነት ምንድን ነው?
እርሳቸውም ቆፍጠን ባለ አነጋገር “ኢትዮጵያዊነት ኩራትና ትህትና ነው” አሉት። ጋዜጠኛውም ቢሆን የዋዛ አልነበረምና “ይቅርታ ያድርጉልኝ ጃንሆይ ይሄ ሃምብልነስ እና ፕራውድነስ የሚሉት ነገር እርስ በርሱ የሚጣረስ ማንነት አይመስልዎትም?” የሚል ጥያቄ ያስከትላል። ንጉሱም እንዲህ አሉ “አየህ አንድ በጣም ተራ የምትለው ገበሬ ቤት በእንግድነት ብትሄድ ያለውን አብልቶ፤ እግርህን አጥቦ፤ ያጠበውን እግርህን ስሞ፤ አልጋውን ላንተ ለቆ እርሱ ግን መሬት ላይ ይተኛል። በዚያው ልክ በሚስቱ፣ በርስቱና በሃገሩ ላይ ብትመጣበት ደግሞ በግንባርህ ላይ ጥይት ይቆጥርልሃል፤ ስለዚህ አይጋጭም፤ ነገር ግን ይሄንን ነገር ለመረዳት አንተ ራስህ ኢትዮጵያዊ መሆን አለብህ” ነበር ያሉት። ኢትዮጵያዊነትን ለመረዳት ኢትዮጵያዊ መሆንን ይጠይቃል፤ኢትዮጵያዊነት ረቂቅ ነውና!!!

Comments

Popular Posts