የጉራ ጦርነት የግብፅ የተደመሰሰበት እዉነታ !! Part 1
ግብፃውያኑ ኢትዮጵያን ለመውረር ሙከራ አደረጉ፡፡ በዚህን ጊዜ የግብፅ መንግስት 17,000 ያህል ወታደሮችን ይዞ ነበር (በወቅቱ ከፍተኛ የሆነ የጦር ሠራዊት ነዉ)፡፡ በዚህን ጊዜ በሬቲብ ፓሻ ስር ያለው የግብፅ የእስማኤል ፓሻ ኃይሎች በታህሳስ 14 ቀን 1875 ወደ መሰዋ ይደርሳሉ፡፡ይህም ሠራዊት እ.ኤ.አ. በማርች ወር ወደ ጉራ ሸለቆ አቅራቢያ በመድረስ ክፍለ ጦሩን በሁለት ከፈሉት ማለትም በሁለት በኩል ለማጥቃት እንድያመቻቸዉ ፣ አንደኛው በጉራ ሜዳዎች እና ሁለተኛው የከሀያ ክሆር ተራሮችን ጥቂት ኪሎ ሜትሮችን አለፍ ብሎ አሰለፉ። በወቅቱ ኢትዮጵያውያኖች በጠቅላላዉ ከ50 ሺህ እስከ 60,000 ያህል የጦር ኃይል ያላቸው ቢሆኑም ግን በአንድ ጊዜ በጦር ሜዳ በፍጥነት ወደ ዉጊያ የሚገቡ 15,000 ወታደሮች ናቸዉ ይህም ቁጥር እንደዚህ የሆነዉ በወቅቱ በነበረዉ የዉጊያ ስልት ነዉ፡፡የግብፅ ጦር በድጋሜ ኢትዮጵያን ለመዉጋት መምጣቱን የሰማዉ የኢትዮጵያ መንግስት ወደ 15,000 የሚጠጉ Stand By የኢትዮጵያ ወታደሮችን ብቻ እ.ኤ.አ. መጋቢት 7 ፣ 1875 በሁለት ጎራ የተከፈለዉን የግብፅን ጦር ለመዋጋት በመጀመሪያ ላይ ጉራ የመሸገውን ወደ 7700 የምያክለዉን ሠራዊት እንድዋጋና በኋላም የሸሸ በማስመሰል በከሀያ ክሆር በተደበቀዉ ቀሪ የግብፅ ጦር ኢትዮጵያውያንን በቀላሉ ለመምታት ነበር፡፡ የኢትዮጵያውንም ኃይል የሚመራዉ በራስ አሉላ ነበርና በወቅቱ በኢትዮጵያን ላይ ድብቅ ጦርን በማየት የመሸሽ ሁኔታ የታየ ቢሆንም ራሱን የቻለ የጦርነት ስልት ነዉና እንደገና ያፈገፈገዉ የመሳላቸዉ የግብፅ ጦር ለማጥቃት በመጋቢት 10 ቀን ሁለተኛውን ጥቃት ፎርት ጉራ ላይ ሰነዘሩ ፡፡ የሞት ድግስ የተደገሰላቸዉ የግብፅ ሠራዊት ቀለበት ዉስጥ በማስገባት የማያዳግም ድል የኢትዮጵያ መንግስት ጉራ ላይ ድል ተጎናጽፏል፡፡

Comments

Popular Posts