የጉንደት ጦርነት ግብፅ የተደመሰሰበት እዉነታ!! Part 2
በጉራ የተሸነፉት ግብፃውያኑ እልህ ይዞዋቸዉ በተለየ ሁኔታ ጦራቸዉን ይዘዉ በመምጣት እንደገና ኢትዮጵያን ለመውረር ሙከራ አደረጉ፡፡ በአራኪል ቤይ እና በዴንማርክ ኮሎኔል አህሬንድር የሚመራው የግብፃውያን ጦር በቀድሞ የኢትዮጵያ ኤርትራ ክፍለ ሀገር በኩል የባህር ዳርቻችንን የሆነዉን ንብረታችንን (አሁንም ንብረታችን ነዉ ብዬ በግሌ አምነዋለዉ) ወረሩት፡፡ በዚህን ጊዜ ነበር በዚህ አዉራጃ የተነሳዉን ውዝግብ የሰማዉ የኢትዮጵያ የወቅቱ መሪ አጼ ዪሐንስ ጦራቸዉን ይዘዉ ወደ ስፍራዉ ያቀኑት በእርግጥም በሰላያቸዉ በኩል የደረሳቸዉ መልዕክት ትክከለኛ መሆኑን አረጋገጡት ፣ ይህንንም ተከትሎ በአጼ የዮሃንስ የምመራዉ ጦር እና በእስማኤል የምመራዉ የግብፅ ሰራዊት እ.ኤ.አ. በታህሳስ ወር 16 ፡ 1876 ጥዋት ላይ ጉንደት ላይ ተዋጉ። በዚህን ጊዜ ነበር ጥቃት ለመፈጸም ግብፃውያኑ እጅግ ብዙ የሆነዉን ጥምር ጦራቸዉን ይዘዉ በመጡበት ሁኔታ ጀግናዉ የኢትዮጵያ ሠራዊት ባለዉ ልምድ እጅግ ጠባብ በሆነ መንገድ ማለትም በሁለት ተራራ ዉስጥ እንድያልፉ በማድረግ በሚገርም ሁኔታ ወረሩዋቸዉና ድል አደረጓቸዉ፡፡ ይህም የሆነዉ የኢትዮጵያ ጦረኞች ከተሸሸጉበት ሸለቆ በመውጣት በግብፆች አምድ ላይ በፍጥነት ጥቃት በመሰንዘር ልዩ በሆነ የዉጊያ ስልት ሙሉ በሙሉ የግብፅን ጦር ደምስሰዋል፡፡ በወቅቱ የግብፅ ኃይል ሙሉ በሙሉ ተደመሰሰ፡፡ ይህም ኢትዮጵያዊያን ግብፅን ሙሉ በሙሉ ልታጠፋት ነዉ የምል የፍራቻ ወሬ በግብፅ ሀገር በወቅቱ መናፈሱ ታሪክ ይነግረናል፡፡ የሞት ድግስ የተደገሰላቸዉ የግብፅ ሠራዊት ቀለበት ዉስጥ በማስገባት ድጋሜ የማያዳግም ድል የኢትዮጵያ መንግስት ጉንደት ላይ ድል ለሁለተኛ ጊዜ ተጎናጽፏል፡፡

Comments
Post a Comment
Thank You!!